Friday, August 12, 2022
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) መንግሥት መንገደኞች ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመግባት መብታቸውን እንዲያስከብር እና በከተማዋ ዙሪያ ባሉ ፍተሻ ኬላዎች ላይ መንገደኞችን የሚያጉላሉ፣ የሚደበድቡና የሚያስሩ እንዲሁም ከመንገደኞች ጉቦ የሚቀበሉ የጸጥታ ኃይል አባላትን በሕግ እንዲጠይቅ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኢሰመጉ ከአንድ ወር ወዲህ ከአማራ ክልል በተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ መንገደኞች ከከተማዋ ዙሪያ የፍተሻ ኬላዎች ላይ ጸጥታ ኃይሎች መታወቂያቸው እያዩ ወደመጡበት እየመለሷቸው እና ፍተሻ ኬላዎች ላይ እያጉላሏቸው መሆኑን መረጃ ደርሶኛል ብሏል።
ኢሰመጉ መንገደኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡና እንዲንገላቱ እየተደረጉ ያሉት፣ በከተማዋ ዙሪያ ባሉት ሸኖ፣ አለልቱ፣ በኪ፣ ሰንዳፋ እና ለገጣፎ የፍተሻ ኬላዎች ላይ መሆኑን በመግለጫው ጠቅሷል። ጸጥታ ኃይሎች መንገደኞችን የሚያሳልፉት የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል መታወቂያ የያዙ ከሆኑ ብቻ እንደሆነ የገለጸው ድርጅቱ፣ ባንዳንድ የፍተሻ ኬላዎች ላይ መንገደኞችን ለማሳለፍ ጸጥታ ኃይሎች ጉቦ እንደሚጠይቁ መረጃ እንዳለው ጠቁሟል።
ነሐሴ 4 ላይ ከወልድያ-አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር ያለው ኢሰመጉ፣ በነጋታው ግን መንገዱ መከፈቱን አረጋግጫለሁ ብሏል። ኢሰመጉ ነሐሴ 3 ላይ ሰላም ሚንስቴር እና ትራንስፖርት ሚንስቴር በጉዳዩ ላይ በጽሁፍ ማብራሪያ እንዲሰጡት መጠየቁንም ጠቅሷል። ሆኖም ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር፣ ከሚንስቴሮቹ የጠየቀውን የጽሁፍ ማብራሪያ እስኪያገኝ ሳይጠብቅ፣ ይህን መግለጫ ለማውጣት መገደዱን ድርጅቱ ጨምሮ ገልጧል።
https://amharic-zehabesha.com/archives/176569
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment