የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከምትገኘው ቆቦ ከተማ ለቅቆ መውጣቱን መንግሥት አስታወቀ።የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 21፣ 2014 ዓ.ም እንዳስታወቀው “የህዝብን ፍጅት ለማስወገድ ሲባል” መከላከያ የቆቦ ከተማን መልቀቁን ገልጿል።
የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ "በጸረ ማጥቃት ዘመቻ" የቆቦን ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የመንግሥት ኮሚዩኑኬሽን መግለጫ ህወሃት የቆቦ ከተማን ከውጭ “በብዙ አቅጣጫ” እያጠቃ አንደሆነ ገልጾ “የህዝቡን ደህንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል” ብሏል።
በዚህም የተነሳ "መከላከያ የቆቦ ከተማን ለቆ ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል" ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ” የተከፈተባቸውን ጥቃት ለመከላከል በተደረገ የጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማን ጨምሮ ጉጉውዶ፣ ፎኪሳ፣ ዞብል፣ መንደፈራ፣ሮቢት፣ ሽዎች ማርያምና ተኮሎሽ የሚባሉ ስፍራዎችን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።
https://amharic-zehabesha.com/archives/176746
Sunday, August 28, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment