Thursday, August 4, 2022

እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ
እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን በአፋር ክልል የጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርጫፍ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ።

የጣቢያዉ አስተባባሪ ኮማንደር አህመድ ሳልህ እንደገለጹት፤ በፍተሻ ጣቢያዉ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ ነዳጅና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች እየተያዙ ነው።

ባለፈዉ ሳምንትም በጣቢያዉ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ መያዙን አስታውሰው፤ ዛሬ ጠዋት 3 ሰአት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-A10298 የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር 23634 በሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ውስጥ 2 ሚሊዮን 280 ሺህ 640 ብር ሊያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው የእርዳት እህል ጭኖ ሲጓዝ እንደነበረም አመልክተዋል።

ከገንዘቡ በተጨማሪ የወርቅ ሚዛንና ሌሎች ቁሳቁሶችም በተሽከርካሪው ውስጥ በጣቢያው የፍተሻ ሰራተኞች ተይዛል።

መኪናዉና አሽከርካሪዉ በህግ ቁጥጥር ስር ዉለዉ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸዉ እንደሚገኘ የጣቢያ አስተባባሪዉ ኮማንደር አህመድ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

(ኢ ፕ ድ)
https://amharic-zehabesha.com/archives/176443

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...