Wednesday, July 27, 2022

ንስሐ በሌለበት የሚያርግ ምስጋና የለም - ዓባይነህ ካሤ - ዲን
ጠሚሩ አሁንም እንደዞረባቸው ሁሉ ላዙርባችሁ አመስጋኝ እንሁን በሚል "ስብከት" ከጠፉበት ተከስተዋል። ፓስተርነታቸው አገርሽቶባቸው ነው የተመለሱት።

ነቢዩ ያለውን ላስታውስ፦

"እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል። ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተሟገቱ።" ኢሳ ፩: ፲፭ - ፲፯።

ሌላም ልጨምር

"የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።" አሞ ፭: ፳፪-፳፬።

መጽሐፋችን የሚለው እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ - ከሕፃናት እና ከሚጠቡ አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ነው። መዝ ፰፡፪። ወዲህም የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ ልብ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም ይላል። መዝ ፶፡፲፯።

ሲጠቃለል

የኀጥአን መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው። ምሳ ፳፩፡፳፯።

ስለዚህ ጠሚር በአቋራጭ ለመበልጸግ እንዲሚያስቡት በአቋራጭ በእግዚአብሔር ለመሰማት የሚችሉበት ዕድል የለም። ታጠቡ ተብሏል። ዘልሎ ምስጋና የለም። እንዲያው ዙሪያ ጥምጥም ከሚለፉ ንስሐ ይግቡ ንስሐ እንግባ።

እጅዎ ላይ ብዙ ንጹሕ ደም ይጮኻል!!!

--------------------------------------------------------------------------
https://amharic-zehabesha.com/archives/176268

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...