Monday, July 11, 2022

መረጃ # በአጣዬ ቅርብ ርቀት የሚገኙ መንደሮች በኦነግ/ሽኔ እየተቃጠሉ ናቸው!!

መረጃ # በአጣዬ ቅርብ ርቀት የሚገኙ መንደሮች በኦነግ/ሽኔ እየተቃጠሉ ናቸው!!
ከአጣዬ በቅርብ እርቀት የሚገኙ መንደሮች—ማዋዬና፣ አርሶ አምባ፣ ሞላሌ፣ ዘንቦ፣ በር ግቢ፣ ሺህ ሰማን—-በኦሮሞ ብልፅግና በሚደገፈው ኦነግ/ሸኔ እየተቃጠሉ ናቸው።

በቦታው የኦነግ ባንዲራ ተሰቅሏል። በርካቶች ቆስለዋል፤ ቆስለዋልም፣ መንገዶች ተዘግተዋል፣ ተሽከርካሪ ማለፍ አይችሉም።

ከጭፍጨፋው ያመለጡት ወደ ዳገታማው የመንዝ አካባቢ እየሸሹ ነው። በአሁኑ ሰዓት የአማራ ልዩ ኃይል በአካባቢው የለም። ከጨፍጫፊዎች ውጭ ሌላ ታጣቂ ሃይል በስፍራው የለም።

ባልደራስ ለእውነተኛ



# የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች ደም እንዳይለግሱ ተከለከሉ!!


/


'ወደ ፍቅር' የተሰኘው የክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች ማህበር በብሔራዊ ደም ባንክ በኩል ደም እንዳይለግስ ተከልክሏል።


"ሺህ ሆነን የሺህዎችን ህይዎት እንታደግ" በሚል መርህ ትናንት፣ እሁድ ፣ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ሊደረግ የታሰበው የደም ልገሳ የተከለከለው 'ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ ነው' መባሉን ማህበሩ አስታውቋል።


"ከየትኛውም ነገድ እና የፖለቲካ እስቤ ነፃ መሆን ከሚጠበቅባቸው እና የሰብዓዊነት ሥራ ብቻ ይሰራባቸዋል ተብለው ከሚታሰቡት አንዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደም ባንክ ሆኖ ሳለ፣ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ተቋም ላይ ይህን ዓይነት የፖለቲከኞች ፍላጎት ማስፈፀሚያ ሆኖ መገኘቱ ቅር የሚያሰኝ እና የሰብዓዊ ስራዎች ላይ ለተሰማሩትም እንቅፋት መሆን እጅግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ለወደፊትም እንዲህ ዓይነት ተግባሮች ተቋሙ ከተቋቋመበትም ከቆመለትም ዓላማ እና እሳቤ ውጪ ያፈነገጠ በመሆኑ፣ በቶሎ ሊታረም እና ሊደገምም የማይገባው ነው ብለን በፅኑ እናምናለን" ብሏል ወይ ፍቅር ማህበር።


ለደም ልገሳው ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጿል።


/




Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 


https://amharic-zehabesha.com/archives/174559

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...