Saturday, July 23, 2022

4ኛ ቀኑን የያዘው የለንደኑ የርሃብ አድማ ቀጥሎ መዋሉን ለመመልከት ተችሏል

4ኛ ቀኑን የያዘው የለንደኑ የርሃብ አድማ ቀጥሎ መዋሉን ለመመልከት ተችሏል
ይህ የርሃብ አድማ በውስን አማራዎች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተደረገ ሲሆን አላማውም በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት ማውገዝ፣ እንዲቆም መጠየቅ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ መንግስታዊ መዋቅር ጭምር ተሳትፎ እያደረገበት ያለው የዘር ፍጅት መሆኑን የዩኬ መንግስት ተገንዝቦ ከንጹሃን ጎን እንዲሰለፍ ለማሳሰብም ነው።





በተለያዩ ጊዜያቶች ለኢትዮጵያ መንግስት የሚደረጉ ድጋፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአማራ ላይ ለሚፈጸሙ የጅምላ ፍጅት እንደሚውሉ ግንዛቤ ተወስዶ ጫና ማድረግ እንዲችሉም ተጠይቋል።

4ተኛ ቀኑን በያዘው የርሃብ አድማ ከሚሳተፉት መካከል በተለይም ሮማን ተስፋዬ ተዳክማ ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት በሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ስትደገፍ ታይታለች።


፤ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችም ድጋፍ ሲሰጡ ተስተውሏል።

ከሲዊትዘርላንድ የርሃብ አድማ ለማድረግ ወደ እንግሊዝ ለንደን ያቀናችው የስቶፕ አምሃራ ጄኖሳይድ ዳይሬክተር ዮዲት ጌዲዮን በማህበራዊ ትስስር ገጿ እንዳጋራችው የአማራን የዘር ፍጅት በመቃዎም በሎንዶን፤ እንግሊዝ እየተደረገ ያለው የርሀብ አድማ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።

"አለን ሰላም ነን።እኔ ውሀ ዛሬ ትንሽ ጠጥቻለሁ። ያየሽይራድ ግን እምቢ አለች። ትንሽ እየደከመች ነው። ግን እየተከታተልናት ነው።" የሚል መልዕክቷን አጋርታለች።

መንግስታዊ የአማራው የዘር ፍጅት ይቁም!፣

በአማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት በገለልተኛ ወገን ይጣራ!፣

ፍትህ ለዘር ፍጅት ሰለባ ለሆኑ አማራዎች የሚሉና የመሳሰሉ መልዕክቶችም እየተላለፉ ነው።


አዲስ ሚዲያ
https://amharic-zehabesha.com/archives/176192

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...